በፕላን የሚመሩና ደረጃቸውን የጠበቁ ተወዳዳሪ ከተሞች ለመፍጠር ርብርብ እየተደረገ ነው

You are currently viewing በፕላን የሚመሩና ደረጃቸውን የጠበቁ ተወዳዳሪ ከተሞች ለመፍጠር ርብርብ እየተደረገ ነው

AMN- ህዳር 6/2018 ዓ.ም

በፕላን የሚመሩና ደረጃቸውን የጠበቁ ተወዳዳሪ ከተሞች ለመፍጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።

በአፋር ሰመራ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 10ኛው የከተሞች ፎረም መልዕክት ያስተላለፉት ሚኒስትሯ፣ ፎረሙ የከተሞችን የአሁንና የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰን መሆኑን ተናግረዋል።

ከተሞች በተሰጣቸው የለውጥ ሚና የአሁኑን እና የወደፊቱን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ ስራዎች በርብርብ እየተሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከለውጥ በኋላ እንደ ሀገር ለከተሞች በተሰጠው ትኩረት ስኬታማና ተምሳሌት የሆኑ የከተማ ልማት ስራዎች መሰራታቸውንም ወ/ሮ ጫልቱ ገልጸዋል።

የከተሞች ልማት በአስተማማነኝ ሁኔታ የሚረጋገጠውና አቅም የሚፈጠረው በከተማ ህዝብና ባለድርሻ አካላት ኣካታች ርብርብ ሲደረግ ነው ያሉት ሚኒስተሯ፣ ለዚህም ትብብርን በማላቅ መስራት እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።

10ኛው የከተሞች ፎረም የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጉዳዮች ላይ ምክክር የሚደረግበት፣ የልምድ ልውውጥ እንዲሁም የምርምርና ጥናት ስራዎች የሚቀርብበት መሆኑም ተመላክቷል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review