በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ስዊድንን ያስተናገደችው ስዊዘርላንድ 4ለ1 አሸንፋለች።
ብሪል ኢምቦሎ ፣ ግራኒት ዣካ ፣ ዳን ንዶይ እና ጆሀን ማንዛንቢ የስዊዘርላንድን አራት ግቦች አስገኝተዋል።
በአዲሱ አሰልጣኝ ግርሀም ፖተር እየተመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ስዊድኖች ቤንጃሚን ኒይግረን ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ምድብ ሁለትን በ13 ነጥብ የምትመራው ስዊዘርላንድ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን ለማግኘት ተቃርባለች።
በቀጣይ ማክሰኞ በ10 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችውን ኮሶቮ ስትገጥም አንድ ነጥብ ማግኘት በቂዋ ይሆናል።
በምድብ ሦስት ዴንማርክ ከቤላሩስ 2ለ2 ሲለያዩ ፣ ግሪክ ስኮትላንድን 3ለ2 አሸንፋለች።
ምድቡን ዴንማርክ በ11 ነጥብ ስትመራ ፣ ስኮትላንድ በ10 ትከተላለች።
ሁለቱ ሀገራት ቀጥታ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎን ለማግኘት የፊታችን ማክሰኞ በስኮትላንድ ሀምፕደን ፓርክ ይጫወታሉ።
በሸዋንግዛው ግርማ