የከተሞች ፎረም የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ የከተሞችን እድገት ያፋጥናል

You are currently viewing የከተሞች ፎረም የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ የከተሞችን እድገት ያፋጥናል

AMN– ሕዳር 07/2018 ዓ.ም

የከተሞች ፎረም የርስ በርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ የከተሞችን እድገት እንደሚያፋጥን

የፎረሙ ተሳታፊዎች ገለጹ፡፡

በ10ኛው የከተሞች ፎረም 143 ከተሞች ሰመራ ሎጊያ ከተማ የከተሞቻቸውን ጸጋዎችና መገለጫዎቻቸውን ለእይታ ይዘው ቀርበዋል።

በከተሞች ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በተዘጋጀው ኤግዚቪሽን እንዲያስተዋውቁ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

የኤግዚቪሽኑ ተሳታፊዎች ለኤኤምኤን እንደተናገሩት ፎረሙ የርስ በርስ ልምድ ልውውጥ ያደረጉበት ሲሆን ይህም የተቀራረበ የከተሞች እድገት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

ፎረሙ በከተሞች የሚሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች፣ የስማርት ሲቲ ትገበራዎች፣ የአገልግሎት ሪፎርሞች፣ የኢንዱስትሪላይዜሽን ሽግግሮች እና የኢንቨስትመንት አማራጮቻቸው የቀረቡበት ነው።

የከተሞች እድገት ለኢትዮጵያ ልህቀት በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ያለው 10ኛው የኢትዮጽያ ከተሞች ፎረም እስከ ህዳር 10 ይቆያል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review