ኖርዌይ ከ28 ዓመት በኋላ ለዓለም ዋንጫ አለፈች

You are currently viewing ኖርዌይ ከ28 ዓመት በኋላ ለዓለም ዋንጫ አለፈች

AMN – ህዳር 08/2018 ዓ/ም

ኖርዌይ ጣልያንን በማሸነፍ ከ28 ዓመት በኋላ ወደ ትልቁ መድረክ ተመልሳለች።

በሳን ሲሮ በተደረገው ጨዋታ ኖርዌይ 4ለ1 አሸንፋለች። ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ ፣ አንቶኒዮ ኑሳ እና ስትራንድ ላርሰን ሌሎች ግቦችን አስቆጥረዋል።

የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ሃላንድ በማጣሪያ ጨዋታዎች 16 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል። በዘንድሮ የውድድር ዓመት ለሀገሩ እና ለክለቡ ያስቆጠራቸውን የግብ ብዛቶች ደግሞ 32 አድርሷል።

ምድብ ዘጠኝ ላይ የተደለደለችው ኖርዌይ ስምንቱንም የማጣሪያ ጨዋታዎች አሸንፋ ደማቅ ታሪክ አፅፋለች። በኖርዌይ በደርሶ መልስ የተሸነፈችው ጣልያን በጥሎ ማለፍ ዙር ትሳተፋለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review