የሰመራ ኮሪደር የከተማዋን ገጽታ ከማስዋቡ ባለፈ የክልሉ ባህልና ጸጋ የተገለጠበት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ

You are currently viewing የሰመራ ኮሪደር የከተማዋን ገጽታ ከማስዋቡ ባለፈ የክልሉ ባህልና ጸጋ የተገለጠበት መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ

AMN ህዳር 9/2018 ዓ.ም

የአፋር ክልል ርዕሰ መዲና የሆነችው ሰመራ ከተማ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ውበቷን የጨመሩ ለነዋሪዎች ሞቾትን የሰጡ መሰረተ ልማቶች ተከናውነዋል።

በእነዚህ የኮሪደር መሰረተ ልማቶችም የከተማዋ ነዋሪዎች ነፋሻማ አየር የሚያገኙበት ምሽቱን ደግሞ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚያሳልፉባቸው የመዝናኛ አማራጮችን ተፈጥረዋል።

ኤኤምኤን ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ሰመራ ትላንትና ዛሬ ለየቅል ነች ብለዋል።

ጥቁር አስፖልትና አቧራ ከማየት ውጪ ትላንት ምንም ልማት አልነበራትም ያሉት ነዋሪዎቹ ዛሬ ግን የተዘረጉት ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች ፣የሳይክል መስመር፣የዘመኑ የመብራት መስመሮች፣የህጻናት መጫዎቻዎች፣የመዝናኛ ፓርኮችና አረንጓዴ ቦታዎቻ ከተማዋን ልዩ ውበት ሰጥቷታል ብለዋል።

ከመዝናኛነትና ምቾትን ከመስጠት ያለፈው የኮሪደር ልማት የክልሉን ባህልና እሴት የሚገልጹ ልማቶች መሰራታቸው ደግሞ እንዳስደነቃቸው ገልጸዋል ነዋሪዎቹ።

የሰመራ የኮሪደር ልማት ከአዲስ አበባ ከተማ የተገኘውን ልምድ በመውሰድ የተጀመረ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር የ2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው።

በ2ኛው ዙር ደግሞ 3.4 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት በመከናወን ላይ ነው።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review