በየዓመቱ በህዳር ወር ላይ ቆሻሻን የማቃጠል ተግባር እየቀነሰ ቢመጣም ችግሩ ሙሉ በሙሉ አለመወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር አጀንሲ እና የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቁ ፡፡
የባለስለጣኑ የአካባቢ ሕግ ተከባሪነት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ጉደታ እንደተናገሩት ፣ ቆሻሻን የማቃጠል ልምምድ አካባቢን ከማጽዳት ይልቅ አከባቢን የሚበክል በመሆኑን ገልፀዋል።
ፕላስቲክ ቆሻሳችን ማቃጠል እንደ ካንሰር ላሉ በሽታዎች እደሚዳርግ በመገንዘብ፤ ህብረተሰቡ በራሱ እና በአከባቢው ላይ ከሚደርስ አደጋ መታደግ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ቆሻሻን የማቃጠል ጉዳዩ ላይ ህብረተሰቡ የባህሪ ለውጥ በማምጣት ተግባሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ይገባልም ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር አጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሙላት ተገኘ በበኩላቸው፣ በህዳር ወር ላይ የሚደረገውን ቆሻሻን የማቃጠል ልምድ ለማስቀረት “ህዳር ሲፀዳ” በሚል ሰፊ የንቅናቄ ስራዎች እየተከናወነ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
ከግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ጎን ለጎን ተግባሩን በሚፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ጠቁመዋል፡፡
በጽዮን ማሞ