የተገነቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወጣቱ ትውልድ እንዲጠቀምባቸውና ሁልጊዜ ክፍት እንዲሆኑ የማስተዳደሪያ መመሪያ ተዘጋጀ

You are currently viewing የተገነቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወጣቱ ትውልድ እንዲጠቀምባቸውና ሁልጊዜ ክፍት እንዲሆኑ የማስተዳደሪያ መመሪያ ተዘጋጀ

AMN_ ህዳር 11/2018 ዓ.ም

የተገነቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወጣቱ ትውልድ እንዲጠቀምባቸውና ሁልጊዜ ክፍት እንዲሆኑ የማስተዳደሪያ መመሪያ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮው ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተገነቡ ማዘውተሪያ ስፍዎች ከአንድ ሺ 500 በላይ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የስፖርት ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትና የስፖርት ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ውስጥ ተገንብተው ወደ አገልግሎት የገቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ተዟዙረው ተመልክተዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ለማዘውተሪያ ስፍራ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት ቢሰጥም አስተዳደር ላይ ግን ክፍተት መኖሩን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን ይገልጻሉ፡፡

የተገነቡ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ወጣቱ ትውልድ እንዲጠቀምባቸውና ሁልጊዜ ክፍት እንዲሆኑ የማስተዳደሪያ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ክፍለ ከተሞች መውረዱን የገለጹት ቢሮ ኃላፊው፣ አንድም የማዘውተሪ ስፍራ ተዘግቶ እንዳይውል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዛሬው ጉብኝት ላይ ከተሳተፉ የስፖርት ባለሙያዎች መካከል አስተዳደር ዘርፍ ውስጥ የሚሰሩ መኖራቸውን የገለጹት አቶ በላይ፤ ጉብኝቱ በእውቀት እንዲመሩ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

ጎብኝዎቹ በበኩላቸው የተመለከቷቸው የማዘውተሪያ ስፍራዎች በየስፖርት ዓይነቱ ብቁና ውጤታማ ተተኪ ለማፍራት የሚያስችሉ መሆኑን ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠቁመዋል፡፡

የቡልቡላ ፓርክን ጨምሮ የተለያዩ ማዘውተሪያ ስፍራዎች በዛሬው ጉብኝት የተዳሰሱ ሜዳዎች ናቸው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review