ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ የወል ድምጽ እና የጋራ ፍላጎት በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ከደቡብ አፍሪካዉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር
መወያየታቸዉን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በቡድን 20 አባል ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ የአስተናጋጃችን ሀገር ፕሬዝደንት ከሆኑት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ተገናኝተናል።
ታሪካዊው የጂ20 ጉባኤ በአፍሪካ ምድር እንደመሰናዳቱ በተለያዩ ጉዳዮች እንዲሁም በጉባኤው የአፍሪካ የወል ድምጽ እና የጋራ ፍላጎት የሚቀርብበትን ሁኔታ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።