ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር መልካም ውይይት ማድረጋቸውን በይፊዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለውም ” በሁለቱም ሀገሮቻችን ቅድሚያ በምንሰጠው በንግድ እና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ባተኮረ የግብርና ማዘመን ሥራ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተነጋግረናል” ብሐዋል።