ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 በኮሪደር ልማት በተሰሩ የህዝብ ማረፊያ ወንበሮች ላይ የታጠቡ ልብሶችን ያሰጡ ግለሰቦችና ተቋም እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታወቀ።
ድርጊቱን ፈጽመው የተገኙ የኮሪደር ልማቱ የመዝናኛ ካፌ እና ሰራተኞቹን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂ በማድረግ ካፌው ተገቢው ቅጣት አስኪቀጣ መታሸጉ ተገልጿል።
ህብረተሰቡ በከተማዋ ውስጥ በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ የኮሪደር ልማቶችና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ መገልገልና መጠቀም እንደሚገባም አስታውቋል፡፡
ደንብ ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ በህጉ መሠረት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታውቋል።