በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደረቅና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ ይቀጥላል

You are currently viewing በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደረቅና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ ይቀጥላል

AMN ጥር 5/2018

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአብዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደረቅና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ አንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ለኤኤምኤን በላከዉ መግለጫ በሚቀጥሉት አሰር ቀናት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ክፍሎች ደረቅና ቀዝቃዛ አየር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብሏል።

የበጋው ደረቅ ጸሃያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚስተዋልና የለሊትና የማለዳው ቅዝቃዛ ከአምስት ዲግሪ ሼልሲየስ በታች እንደሚሆን አመልክቷል።

ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው የሆኑ የደቡብና የደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ደረቅ ሆነው እንደሚቆዩም የትንበያ መረጃው ያመለክታል።

በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ፣ የምዕራብና የመካከለኛው እንዲሁም ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አንጻራዊ የእርጥበት መጠንና የደመና ሽፋን ጥንካሬ ሊኖራቸው እንደሚችል በትንበያው ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review