odsprntoeS75905 4ti04:8afgieM5a umacd791Y8rhf5atlysA101eg9 0 ·

You are currently viewing odsprntoeS75905 4ti04:8afgieM5a umacd791Y8rhf5atlysA101eg9 0 ·

ማንችስተር ሲቲ ከኒውካስትል ዩናይትድ ፦ ለፍፃሜ ለማለፍ የሚደረግ ጨዋታ

AMN ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም

በካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን ያስተናግዳል። በሴንት ጀምስ ፓርክ የተከናወነው የመጀመሪያው ጨዋታ በሲቲ 2ለ0 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

ፍፃሜ የመድረስ የተሻለ እድል ያለው ማንችስተር ሲቲ ሰሞነኛ ብቃቱ ጥሩ አይደለም። በሳምንቱ መጨረሻ 2ለ0 የመራውን የቶተንሃም ጨዋታ አቻ መለያየቱ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ፉክክሩ ላይ ወደ ኋላ መልሶታል።

ሲቲ ፕሪሚየር ሊጉ ባይሳካለት እንኳን ሌሎች ዋንጫዎችን ማሸነፍ ይፈልጋል። በፔፕ ጋርዲዮላ እየተመራ ዋንጫዎችን መሰብሰብ የለመደው ክለብ ባለፈው የውድድር ዓመት ምንም ዋንጫ ሳያሸንፍ ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ማንችስተር ሲቲ በካራባኦ ካፕ ጥሩ ክብረወሰን አለው። በውድድሩ ስምንት ጊዜ ባለድል በመሆን ከሊቨርፑል በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ክለቡ ካሸነፋቸው ስምንት የካራባኦ ዋንጫዎች ውስጥ አራቱን ያስገኘው ፔፕ ጋርዲዮላ ነው።

ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪክ ብቸኛውን የካራባኦ ዋንጫ ያሸነፈው ባለፈው ዓመት ሊቨርፑልን በመርታት ነበር። የኤዲ ሀው ቡድን ይህን ገድሉን ለመድገም ተአምር ይፈልጋል። ምሽት 5 ሰዓት የሚጀምረውን ጨዋታ አሸንፎ በተከታታይ ሁለት ዓመት ለፍፃሜ ለመድረስ የ2ለ0 ውጤቱን መቀልበስ ይኖርበታል።

በድምር ውጤት አሸናፊ የሚሆነው ክለብ በፍፃሜው አርሰናልን በዌምብሌይ ስታዲየም ይፋለማል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review