የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ይጀመራል

You are currently viewing የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 ይጀመራል

AMN – የካቲት 5 ፣ 2018

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ የካቲት 28 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ፡፡

ቦርዱ በተያዘው 2018 ዓ.ም ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ቦርዱ እስካሁን ስለሠራቸው የቅድመ ምርጫ ሥራዎች በተመለከተና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ቦርዱ ቀደም ብሎ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 በሚል ያስቀመጠውን የመራጮች የምዝገባ ሂደት በማሻሻል የካቲት 28 ምዝገባ እንደሚጀመር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል::

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ኃይሉ የክልል ምርጫ ጣቢያ ጽ/ቤት መክፈት፣ ማደረጀትና የሰዉ ኃይል ማሟላት ተከናውኗል ብለዋል::

የዘንድሮውን ምርጫ በቴክኖሎጂ ለማካሄድም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ እጩዎቻቸውን የማስመዝገብ ሥራ ከጥር 1 ጀምሮ እየተከናወነ መሆኑም በመግለጫው ተነስቷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የአየር ሰዓት ክፍፍል ፍትሐዊ ለማድረግ ከወዲሁ ከመገናኛ ብዙኃን ጋር እየተሠራ መሆኑን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡

ከፀጥታ አንጻርም ከመንግሥት ጋር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላት ወርቅ ኃይሉ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በአንዋር አሕመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review