አፈ ጉባኤ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

AMN – ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም

አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ችን ሃይ ጋር የሁለቱን ሀገራት ትብብር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ዓመታት የቆየውን የሁለትዮሽ ትብብር በተለያዩ መስኮች በማጠናከርና በፓርላማዎቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት በማጎልበት ላይ ያተኮረ ነበር።

አምባሳደር ችን ሃይ በበኩላቸው፣ ለተከበሩ አፈ ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አቅርበው፣ የሥራ ዘመናቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review