ማንችስተር ዩናይትድ በኮሞ በሰፊ ውጤት ተሸነፈ

You are currently viewing ማንችስተር ዩናይትድ በኮሞ በሰፊ ውጤት ተሸነፈ

AMN- ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም

የ3ኛ ዙር የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ከኮሞ ጋር ያደረገው ማንችስተር ዩናይትድ 4ለ1 ተሸንፏል።

በሴስክ ፋብሪጋስ የሚመራው ኮሞ ከፍተኛ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ አርጀንቲናዊው አማካይ ኒኮ ፓዝ ሁለት ግቦችን አስመዝግቧል። አናስታሲዮስ ዱቪካስ እና ጃኮቦ ራሞን የኮሞን የበላይነት ያረጋገጡ ተጨማሪ ሁለት ግቦች አስቆጥረዋል። የዩናይትድን ብቸኛ ግብ ተቀይሮ የገባው ጆሹአ ዚርክዜ አስቆጥሯል።

አስደናቂ እድገት ላይ የሚገኘው ኮሞ እኤአ 2008 ማንችስተር ዩናይትድ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሲያሸንፍ የሴሪ ዲ ተሳታፊ ነበር። አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈበት ከሚገኘው የአውሮፓ ትልቁ መድረክ ላይ ታሪክ የማይዘነጋው ድል አስፅፏል።

የቁልቁለት መንገዱን የተያያዘው ማንችስተር ዩናይትድ በሁሉም ውድድር ካደረጋቸው የመጨረሻ ሰባት ጨዋታዎች አንዱንም አላሸነፈም። በአጠቃላይ ካደረጋቸው 11 ጨዋታዎች ድል ያስመዘገበው በሁለቱ ብቻ ነው። የዛሬው ሽንፈት የአሰልጣኙ ማይክል ካሪክን መንበር የሚንጥ ይመስላል።

ኮሞ ከሦስት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ሁለቱን በማሸነፍ ስድስት ነጥብ ሲይዝ፣ አንድ አሸንፎ በሁለቱ ሽንፈት የገጠመው ዩናይትድ ሦስት ነጥብ አለው። በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ጋላታሳራይ ከሜዳው ውጪ ሊልን 4ለ2 አሸንፏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review