ከካዛንቺስ በኮሪደር ልማት የተነሱ ነጋዴዎች ስራቸውን እንዲጀምሩ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ተለዋጭ የመስሪያ ቦታ ተመቻችቷል- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ

You are currently viewing ከካዛንቺስ በኮሪደር ልማት የተነሱ ነጋዴዎች ስራቸውን እንዲጀምሩ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ተለዋጭ የመስሪያ ቦታ ተመቻችቷል- የቂርቆስ ክፍለ ከተማ

AMN – ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

ከካዛንቺስ በ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሱ ነጋዴዎች ስራቸውን እንዲጀምሩ ተለዋጭ የመስሪያ ቦታ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ማመቻቸቱን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በ2ኛው ዙር የኮሪደር ልማት በካዛንቺስ እና አካባቢዋ የሚገኙ በልማቱ ተነሺ የሆኑ ነጋዴዎች በመደበኛነት ተጀራጅተው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ቦታ እስኪመቻች ድረስ በጊዜያዊነት ስራቸውን እንዲጀምሩ ማመቻቸቱን አስተዳደሩ ገልጿል።

ነጋዴዎቹ ተደራጅተው እንዲሰሩ መንግስት 25 ካሬ ሜትር ቦታ የሰጣቸው ሲሆን ቦታው ላይ ግንባታቸውን አጠናቀው ስራ እስከሚጀምሩ በከተማ አስተዳደሩ ጊዜያዊ ቦታዎች ተሰርተው እንደቀረቡ ተገልጿል።

እጣው የተለያዩ 5 ቦታዎችን የያዘ ሲሆን ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ ጀርባ፣ ጋዜቦ ወደ ቡልጋሪያ መንገድ፣ ሀዲድ ከጋዜቦ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ፣ ሀዲድ ጫፍ ጊፍት ሪል ስቴት አካባቢ እንዲሁም ቤተሰብ መምሪያ ጎን እንደሚገኙም ከቂርቆስ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review