አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመፍታት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር በትጋት አቅዶ መስራት ይጠበቅበታል፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ህዳር 3/2017 ዓ.ም

አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመፍታት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር በትጋት አቅዶ መስራት ይጠበቅበታል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳሰቡ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምሯል::

በመድረኩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በግምገማችን እቅዳችንን የከወንበትን መንገድ በመገምገም ጥንካሬዎቻችንን እያስቀጠልን በድክመት የተለዩ ስራዎችን ደግሞ በትኩረት መገምገም ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

በስራዎቻችን ላይ የሚታዩ ድክመቶችን ሳንሸፋፍን መገምገማችን አንዱ የጥንካሬያችን ምንጭ በመሆኑ ብልሹ አሰራር፣ ሌብነት፣ ጉቦኝነት እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ክፍተት በመፍታት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ ለመገንባት ሁሉም አመራር እንዴት አቅዶ ስራን እንዲሁም ሀላፊነቱን እንደተወጣ መገምገም ይገባል ማለታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review