አዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት እየተገነባችና አዳዲስ ለውጦችን እያስመዘገበች ያለች ከተማ ሆናለች-የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር

AMN-ኅዳር 29/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት እየተገነባችና አዳዲስ ለውጦችን እያስመዘገበች ያለች ከተማ መሆኗን የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሪየን ጁሬስካ ተናገሩ፡፡

ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያንና የአብርሆት ቤተመጽሃፍትን ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናችው፡፡

ሀገራቱ በቱሪዝም ፣በቅርስ ጥበቃ፣ ምርምር በወታደራዊ ፣በግብርና እንዲሁም በኢኮኖሚ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማሳደግም እየሰሩ መሆኑ ያታወቃል፡፡

የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለውን የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግም በመሪዎች ደረጃ ባለፈው አመት ጉብኝት መካሄዱ ይታወሳል፡፡

እየተጠናከረ በቀጠለው የሀገራቱ ግንኑነት የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሪየን ጁሬስካ በኢትዮጵያ ይፋዊ ስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካን ቡድናቸውም የአብርሆት ቤተመጽፍትና የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው የተመለከቷቸው የአብርሆት ቤተ መጽሃፍትና የዓድዋ ድል መታሰቢያ አስገራሚ የኪነ ህንጻ ጥበብን የያዙ የሚሰጧቸውም አገልግሎቶች አስደናቂ መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማን ከ7 ከአመታት በፊት እንዲሚያውቋት ያስታወሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተማዋ በፍጥነት እያደገች እና እየተገነባች ያለች መሆኗ እንዳስገረማቸውም ተናግረዋል፡፡

እየተሰሩ ያሉ መሰረተ ልማቶች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ ሆነው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የሁለቱን ሀገራት ድፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትብብርን ለማጠናከርም እየተሰራ መሆኑን ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት፡፡

በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ትብብራቸውን ለማላቅ ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review