
AMN – ታኅሣሥ 9 /2017 ዓ.ም
በኢትዮጵያ በአየር ብክለት ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሚኒስቴሩ የአየር ብክለትን በመቀንስ በ20 30 ተላላፈ ባልሆኑ በሽታዎች የሚሞቱ ዜጎችን ቁጥር በአንድ ሶስተኛ መቀነስ የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡
የአየር ብክለት በርካታ የሰው ልጅ ህይወትን ለሚቀጥፉ የጤና እክሎች ዋነኛ ሰበብ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ጥናቶች በርካታ ናቸው፡፡
በአየር ብክለት ምክንያት ገዳይ የሆኑት እንደ ካንሰር፣ የልብ ህመም እና ስር የሰደዱ መተንፈተሻ አካላት በሽታዎች የስው ልጅ ህይወት እየነጠቁ የሚገኙ ቀዳሚ የዓለም ስጋቶች ሆነዋል፡፡
በአየር ብክለት ምክንያት ተላለፊ ላልሆኑ በሸታዎች በርካቶች እየተጋለጡ እንደሚገኝ የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጀ ድጉማ በዚህም በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ39 ሺህ በላይ ዜጎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህይወታቸው እደሚያጡ ተናግረዋል፡፡

የአየር ብክለት ችግሩ እንዳይባባስ እና ለብክለቱ መነሻ የሆነን የቆሻሻ አወጋገድ ሂደትን ለማዘመን በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረውን ስራ በሃገሪቱ አጠናክሮ ለመቀጥል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝም ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
በዚህ ረገድ ለበርካታ ዜጎች ህልፈት ሰበብ እየሖነ ያለን የአካባቢ ብክለት ለመከላከል በዜጎችና በተቋማት ደረጃ ብክለት ድርሻ ያላቸው እንቅስቃሴዎችና የምርት ሂደቶች መለየታቸውን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ገልጸዋል፡፡
የአየር ብክለትን ለመቀነስ የ5 አመት ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ይህም ጽዱ ኢትጵያን በመፍጠር በ20 30 ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚሞቱ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ያስችላልም ተብሎ ታምኖበታል፡፡
የጤና ሚኒስቴርና የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በጋራ ለሚያስተባብሩት የአምስት ዓመት ፕሮጀክቱ ትግበራ የትራስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር እና ግብርና ሚኒስቴርን ጨምሮ ከተለያዩ 6 አስፈጻሚ ተቋማት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ