ህንድ በብሪክስ ማዕቀፍ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ማሻሻያ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

AMN ህዳር 18/2017 ዓ .ም

ህንድ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት ማሻሻያ በብሪክስ ማዕቀፍ ትብብር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራኢ ተናገሩ።

ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ፣ ኢንቨስትመንት ፣ የልማት ትብብርና ሌሎች ግንኙነቶችን ለማጠናከር ብሪክስ ትልቅ እድል ይዞ መምጣቱን አምባሳደሩ ገልጸዋል።

አምባሳደሩ እንደገለጹት ብሪክስ በማደግ ላይ ያሉ አገሮችን የምጣኔ ሃብት እድገት ለማፋጠንና በአለም አቀፍ መድረክ ያለውን አሰላለፍ በማስተካከል ሚዛን ለመጠበቅ ያግዛል ብለዋል።

ህብረቱ ኢትዮጵያ ከህንድና ከሌሎች አባል አገራት ጋር ትብብርና አጋርነትን ለማጠናከር፣ ልምድና እውቀትን በመለዋወጥ ለመስራት እንደሚያስችላትም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ ዘላቂ ምጣኔ ሃብት በመገንባት ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያከናወነች ያለውን ሪፎርም በብሪክስ ማዕቀፍ ለማገዝ ህንድ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ የምጣኔ ሃብት እድገትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ እያከናወነች ያለውን ተግባር ህንድ በብሪክስ ማዕቀፍ በሁለትዮሽ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review