AMN-መስከረም 20/2017 ዓ.ም
በቀን 500 ለሚሆኑ ህሙማን የዓይን ህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የዳግማዊ ምኒሊክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል፡፡
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ተከተል ጥላሁን እንደገለጹት፣ በሆስፒታሉ የህፃናት እና አዋቂን ጨምሮ ሁሉም የዓይን ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው።
በ2016 በጀት ዓመት 88 ሺህ 796 ለሚሆኑ ታካሚዎች የዓይን ህክምና አገልግሎት መሰጠቱን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ከዚህ ውስጥ 36 ሺ የሚሆኑት የዓይን ቀዶ ህክምና አገልግሎት መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ለማዘመን እና ለማሻሻል የባለሞያዎችን አቅም የማሳደግ እና ዘመኑን የዋጁ ዘመናዊ የህክምና ማሽኖችን ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ዋና ስራ አስኪያጁ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡