ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ስኬታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ስኬታማ አፈጻጸም ተመዝግቧል – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)

AMN – ሚያዝያ 4/2017 ዓ.ም

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ስኬታማ አፈጻጸም መመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀን አፈጻጸም እና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ያለፉት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተገምግሟል።

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በአራቱም ምሶሶዎች የተሻለ ስኬት መመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸው፣ ይህም የ8.4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ለማስዝገብ የተያዘው እቅድ እንደሚሳካ ያመላከተ ነው ብለዋል በሪፖርታቸው።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት መንግስት ምንም ዓይነት ብድር ከብሔራዊ ባንክ አለመውሰዱን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፣ ይህም የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ትልቅ ፋይዳ ማበርከቱን ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review