ትምህርት የዕድገት መሰረት እንዲሁም የለውጥ ቁልፍ መሳሪያ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ 14ኛውን የአፍሪካ መር የትምህርት እና የቴክኖሎጂ ጉባኤን አስጀምረናል ብለዋል፡፡
ታላላቅ ሀገራት ወደ ታላቅነት ማማ የወጡት በተጠናከረ የዜጎች ትምህርት ትከሻ ላይ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፍሪካ የወጣት ትውልድ አህጉር ናት ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ለዚህ ትውልድ ደግሞ ከዓለም ጋር ተስማምቶ እና ተወዳድሮ ለመቀጠል የሚያስችል አቅም የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
በሀገራችን ኢትዮጵያ የትምህርት እና የክህሎት ስልጠናን ማዕከል በማድረግ እየተሰራ ነው ሲሉም አክለዋል በመልዕክታቸው፡፡
ለዚህም የአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የተሻሻሉ መሰረተ ልማቶች እና ጠንካራ የዲጂታል ትስስር እየተዘረጋ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
በአፍሪካ አሁንም የትምህርት እና የዲጂታላይዜሽን ጉዞን በማሳካት በኩል ቀሪ ስራዎች አሉብን ብለዋል፡፡
ለነገው ትውልድ የምናደርገውን የትምህርት እና የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንት በተቀናጀ እና በተቀላጠፈ መልኩ ማከናወን ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጉባኤው ከንግግር ባለፈ ለተግባር የሚያግዙ ምክክሮች ይደረጋሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ይህን ታላቅ ጉባኤ ዕውን እንዲሆን ላበረከታችሁት አስተዋጽዖ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡





See insights and ads
All reactions:
1818