AMN – መስከረም 23/2017 ዓ.ም
ኢሬቻ እሴቱን ጠብቆ በህዝቦች አንድነትና አብሮነት እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊዋ ጀሚላ ሲምቢሩ በዓሉን ለማክበር የተከናወኑ የዝግጅት ሥራዎችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ኢሬቻ የገዳ ሥርዓት መገለጫ የአንድነት፣ አብሮነትና የሰላም በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በጋር በመሆን የሆራ ፊንፊኔን የማጽዳትና ለሥርዓቱ ምቹ የማድረግ ሥራ መሠራቱንም ጠቁመዋል።
በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ ብሎም የሕዝቦችን አንድነት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት በሚያጠናክር መልኩ እንደሚከበርም ገልጸዋል፡፡
በሌንሳ ሆርዶፋ