ለመጀመርያ ጊዜ እየተደረገ በሚገኘው ግራንድ ስላም ትራክ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል ።
በኪንግስተን በተደረገው በወንዶች 3000ሜትር አትሌት ሀጎስ ገብረ ሂወት 7: 51.55 በመግባት አሸንፏል ፣ በመጀመርያው የ5000 ሜትር ረጅም ርቀት አራተኛ ደረጃ ይዞ መጨረሱን ተከትሎ፣ ያገኘውን ነጥብ 17 በማድረስ በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ አግኝቶ ጨርሷል።
በዛሬው ውድድር ሁለተኛ የወጣው ጥላሁን ሀይሌ በድምር ውጤት አራተኛ ደረጃ ይዞ አጠናቋል።
በሌላ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ሻምፒዮን ሁናለች ።
በጃማይካ ኪንግስተን በተደረገው የ5000 ሜትር ረጅም ርቀት ግራንድ ስላም ትራክ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 14 :54.88 በመግባት በአንደኝነት አሸንፋለች ።
በ3000ሜትር ረጅም ርቀትን በተመሳሳይ በአንደኝነት ያጠናቀቀችው አትሌቷ ፣
ያገኝችውን ነጥብ 24 በማድረስ የርቀቱ ሻምፒዮን ሆናለች።
ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጽጌ ገብረሰላማ 3ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡