ከተሞችን ውብ እና ዘመናዊ ለማድረግ በኮሪደር ልማት የጀመርናቸው እንቅስቃሴዎች ፍሬያማ እየሆኑ ይገኛል:-አቶ አደም ፋራህ

AMN – ታኅሣሥ 4/2017 ዓ.ም

ከተሞችን ውብ እና ዘመናዊ ለማድረግ በኮሪደር ልማት የጀመርናቸው እንቅስቃሴዎች ፍሬያማ እየሆኑ ይገኛል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በአዲስ አበባ ከተማ የታዩ ስኬታማ ተሞክሮዎችን ወደ በለክልል ከተሞች በማስፋት ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው ብለዋል።

ለአብነትም በሀረር ከተማ የኮሪደር ልማት ምን ያህል የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ጉልህ አስተዋፆ እያበረከተ እንደሚገኝ ማየት እንችላለን ሲሉ አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review