የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

AMN-ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቅቋል፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡ የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል፡፡

በዚህም ፤-

1. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

2. አንድነት ብዙሰው ታመነ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

3. አቶ ቁሴ ለታ ዋቅጅራ- የአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

4. አቶ ያብባል አዲስ ጎበዜ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

5.ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

6. አቶ ማሾ ኦላና- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው እንዲያገልግሉ ተሹመዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

#Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review