የኦሮሚያ ባንክ የነዳጅ ግብይት የዲጂታል ክፍያ ለመተግበር የሚያስችል “ሚልኪ” የተሰኘ የነዳጅ ክፍያ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

You are currently viewing የኦሮሚያ ባንክ የነዳጅ ግብይት የዲጂታል ክፍያ ለመተግበር የሚያስችል “ሚልኪ” የተሰኘ የነዳጅ ክፍያ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

AMN – ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም

የኦሮሚያ ባንክ የነዳጅ ግብይት የዲጂታል ክፍያ ለመተግበር የሚያስችል “ሚልኪ” የተሰኘ የነዳጅ ክፍያ መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡

የኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተፈሪ መኮንን ባንኩ ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልጸው በሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በዲጂታል አማራጭ ክፍያ መፈጸም የሚያስችል ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ መተግበሪያ ማስጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

ደንበኞች ነዳጅ በሚቀዱበት ወቅት ዲጂታል የብድር አገልገሎት ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭ ስለመያዙም ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡

የነዳጅ ግብይት በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች በዲጂታል የክፍያ አማራጭ ብቻ እንዲከናወን እየተሰራ መሆኑንን ያስታወሱት ደግሞ የነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ እና የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ሰልማን መሀመድ ናቸው፡፡

ሚሊኪ የተሰኘው የነዳጅ ክፍያ መተግበሪያ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ያስቀመጣቸውን መስፍርቶች ማሟላቱ ፍተሻ ተደርጎበት ወደ ተግባር እንዲገባ ተደርጓል፡፡

በአልማዝ ሙሉጌታ

See insights and ads

Boost post

All reactions:

6868

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review