የኮሪደር ልማቱ በርካታ ፓርኮችን እድሳት እንዲያገኙ እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አድርጓል

You are currently viewing የኮሪደር ልማቱ በርካታ ፓርኮችን እድሳት እንዲያገኙ እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አድርጓል

AMN – ህዳር 2/2017 ዓ.ም

የኮሪደር ልማቱ በርካታ ፓርኮችን እድሳት እንዲያገኙ እና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ነጻነት ዳባ ገልጸዋል።

የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ከተማዋን የሚመጥኑ እና ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ የጎብኝዎችን ቁጥር ማሳደግ እና የተሻለ ገቢ ለማግኘት የሚያስችል ስራ በቅንጅት መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል።

አዳዲስ ፓርኮችን ማልማት እና ነባር ፓርኮችን ደረጃቸውን በማሻሻል ከተማዋ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥኑ እንዲሆኑ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን እሴቶችን በመጨመር ከሀገር ውሰጥ ባለፈ ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች ምቹ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል።

ፓርኮች ደረጃቸውን ጠብቀው መሰራታቸው ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠርም ከፍተኛ አበርክቶ እንዳላቸው የእንጦጦ ፓርክን በማሳያነት በመጥቀስ ገልጸዋል ዋና ዳይሬክተሯ።

የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን በተለይ ፓርኮች ለዜጎች ምቹ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አሁንም የጋራ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን አስጎብኚ ማህበራትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review