AMN- መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
የክሪስታል ፓላሱ አጥቂ ዣን ፊሊፕ ማቴታ በዚህ የውድድር ዘመን ለፓላስ በሁሉም ውድድሮች 15 ጎሎችን አስቆጥሯል።
አጥቂዉ ያገኛቸዉን እድሎች የሚጠቀምበት መንገድም በፓላስ ደጋፊዎች ተወዳጅነትን አትርፎለታል፡፡
በኤፍ ኤ ካፕ 4ኛ ዙር ከሚሊዊል ጋር በነበራቸዉ ጨዋታ ግብ ጠባቂዉ ሊያም ሮበርትስ በፊሊፕ ማቴታ ላይ የሰራዉ አደገኛ ጥፋት ተጨዋቹ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱ የሚታወስ ነዉ፡፡
በግራ ጆሮው ላይ 25 ስፌቶችን ተደርገዉለት ከጉዳቱ ለማገገም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህን ተከትሎ ፊሊፕ ማቴታ በሰጠዉ አስተያየት ስሜት መብዛት እብድ ነገሮችን እንድትሰራ ያደርግሃል” ሲል ተናግሯል፡፡
ማቴታ ባለፈው ሳምንት በማርቤላ ባለዉ የስልጠና ካምፕ ከፓላስ ጋር ተጉዞ በተናጥል ልምምድ ጀምሯል፡፡
የ30 ዓመቱ ሮበርትስ በማህበራዊ ሚዲያ ጥቃት የደረሰበት ሲሆን፣ ወዲያዉ ለማቴታ በስልክ ይቅርታዉን አድርሷል፡፡
ሆስፒታል እያለሁ መልእክት ልኮልኛል ይቅርታዉን ተቀብያለሁ ይህ እግር ኳስ ነው ሊፈጠር ይችላል ብየም መልሸለታለሁ ሲል ፊሊፕ ማቴታ ተናግሯል፡፡
የግብ ጠባቂዉ የሮበርትስ እገዳ ከሶስት ጨዋታዎች ወደ 6 ተራዝሟል ምንም እንኳን ማቴታ ፓላስ ኢፕስዊች ላይ ባደረገው የሊግ ጨዋታ ቢያመልጠውም የክሪስታል ፓላሱ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር የቡድናቸው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መጋቢት 29 ፉልሃም ላይ ለሚያደርጉት የኤፍኤ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ብቁ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ብለዋል።
ማቴታ መቼ እንደገና መጫወት እንደሚችል ሲጠየቅ “አላውቅም አሁንም ከስፔሻሊስቶች እና ከሐኪሜ ጋር እየተገናኘሁ ነው፤ በቅርቡ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል።
የቀድሞ የሜይንዝ እና የሊዮን አጥቂ የፊት ማስክ እንደሚለብስ ተናግሯል “ጭንብል መልበስ አለብኝ፣ “በጣም ምቹ የሆነውን ምርጡን እወስዳለሁ.” ሲል ከስካይ ስፖርት ጋር በነበረዉ ሰፋ ያለ ቆይታ ተናግሯል፡፡
በአለማየሁ ሙሳ