አስገራሚ የመኪና ግዥ

You are currently viewing አስገራሚ የመኪና ግዥ

AMN – ሚያዝያ 20/2017 ዓ.ም

የ36 ዓመቱ እንግሊዛዊ ኢዋን ቫለንታይን በስርቆት ያጣትን መኪና ምትክ ለመግዛት አሰሳ ይጀምራል።

ከመኪና ማቆሚያ ስፍራ ተሰርቃ የተወሰደችበት ባለ ጥቁር ቀለም የ2016 ሞዴል ሆንዳ Civic Type-R መኪና አምሳያን ለማግኘት በብርቱ ይተጋል።

ለመኪናዋ ልዩ ፍቅር እንደነበረው የሚናገረው ኢዋን ፤ መኪናዋ በነጭ ቀለም እንዳለች ሰምቶ ማጣራት ይይዛል።

መኪናዋ ታርጋዋ እና የተሽከርካሪ መለያ ቁጥሯ ቢለይም አጠቃላይ ይዞታዋ ግን ከቀድሞ መኪናው ጋር ተመሳሳይ ስለሆነች በድርድር በ26 ሺህ ዶላር ይገዛታል።

ኢዋን “መኪናዎን ይዤ ቤት ስደርስ አንዳንድ የማውቃቸው የሚመስሉ ምልክቶችን ማስተዋል ጀመርኩ” ይላል።

የኋላ ኮፈኑን ሲከፍት መኪናው በተሰረቀበት ሰሞን ገዝቶ አስቀምጦት የነበረውን የገና ዛፍ ቁርጥራጭ ማየቱ ሲያስደነግጠው ከጎኑ አብሮት ያለው ነገር ደግሞ ጥርጣሬውን አረጋገጠለት።

የተወሰኑ የመኪና መፍቻዎችን “ቴስኮ” በተባለ የሳንድዊች ማስቀመጫ ካኪ ወረቀት ጠቅልሎ የማስቀመጥ የቆየ ልማድ ያለው ኢዋን ማሸጊያውን ሲከፍት እንደ እጁ መዳፍ ከሚያውቃቸው መፍቻዎች ጋር ይገናኛል።

የመኪናውን የአቅጣጫ መመልከቻ “ጂፒኤስ” ሲፈትሽ ደግሞ መዘርዝሩ ውስጥ የእርሱ፣ የወላጆቹ እና የጓደኛው የመኖሪያ ቤት መዳራሻ እንደተሞላ ነው።

ኢዋን መኪናውን ወደ ሆንዳ አከፋፋይ ወስዶ ባስደረገው የቴክክኒክ ምርመራ በስርቆት ያጣው የቀድሞ መኪናው መሆኑን አረጋግጧል።

የቀድሞ መኪናውን የሸጠለት ባለ ጋራዥ መኪናው የተሰረቀ መሆኑን ያውቅ ነበር የሚል እምነት እንደሌለው የገለጸው ኢዋን ቀሪ የህግ ሥራዎችን ፖሊስ እንደያዛቸውም ዩፒአይ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review