የኢፌዴሪ መከለከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢንጂነር ) በቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ የተመራውን ከፍተኛ ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ኢንጂነር አይሻ በሁለቱ አገራት መካካል በወታደራዊና ፀጥታ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ሁለቱ አገራት የጋራ እሴት፣ ታሪክና የባህል መመሳሰል ያላቸው በመሆኑ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ገልፀውላቸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት በወታደራዊ ስልጠና፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ልውውጥና በመሳሰሉ መስኮች ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ለዚሁ እንደሚሰሩ መናገራቸዉን ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡