አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ
AMN-የካቲት 12 ቀን 2017 አ.ም
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች ይደረጋሉ፡፡
ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ በስፔን መዲና ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
የኢትሃዱ ጨዋታ በማድሪድ 3ለ2 አሸናፊነት በመጠናቀቁ ሎስ ብላንኮዎቹ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት የተሻለ እድል ይዘው የሚያከናውኑት ጨዋታ ነው፡፡
ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት ሲገናኙ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ብቻ ለ14ኛ ጊዜ ነው፤በሁሉም ውድድሮች ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ፤በሻምፒዮንስ ሊግ ብቻ 13 ጊዜ በተገናኙበት ጨዋታ አራት አራት ጊዜ ሲሸናነፉ በቀሪዎቹ አምስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ማድሪድ የባለፈው ዓመቱን ጨምሮ ሶስት ጊዜ ሲቲን ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አስወጥቶታል፤ 15 ጊዜ የእንግሊዝ ክለቦችን ከመድረኩ በማሰናበትም፤ ከጀርመን ክለቦች ቀጥሎ የሚበረታባቸው ናቸው፡፡
ማንችስተር ሲቲና ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሲገናኙ የዘንድሮው ለአራተኛ ተከታታይ ዓመታት ነው፤ ይህም በአራትና ከዚያ በላይ ተከታታይ ዓመታት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የተገናኙ አራተኛ ባለ ታሪኮች ሆነዋል፡፡
ዲፖርቲቮ ላ ካሩኛ ከጁቬንቱስ ጋር ከ2001 እስከ 2004፣ ቼልሲ ከሊቨርፑል ጋር ከ2005 እስከ 2009 እንዲሁም አትሌቲኮ ማድሪድ ከሪያል ማድሪድ ጋር ከ2013 እስከ 2017 በተከታታይ ዓመታት በመገናኘት ታሪካቸው ሰፍሯል፡፡
ማንችስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ ጠንካራውን ኒውካስትል ዩናይትድን 4ለ0 አሸንፎ እንዲሁም ማድሪድ በላሊጋው ከኦሳሱና ጋር አቻ ተለያይቶ የሚገናኙበት ጨዋታ ነው፡፡
ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ በፊት ከቢቢሲ ስፖርት ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ካርሎ አንቼሎቲ ‹‹ከፔፕ ጋርዲዮላ ጋር መጫወት ደክሞኛል›› ብለዋል፤ጋርዲዮላ ከዓለማችን ድንቅ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ነው ብለዋል ካርሊቶ ሳቅ በተቀላቀለበት አስተያየታቸው፡፡
ለምሽት 3 ሰዓት ሩብ ጉዳይ የሚጀመረው የቦርሲያ ዶርትሙንድና ስፖርቲንግ ሊዝበን ጨዋታ የዛሬ መክፈቻ ሲሆን ፔ ኤስ ጂ ከብሬስት እና ፒ ኤስ ቪ ከጁቬንቱስ ደግሞ ከምሽቱ 5 ሰዓት ጀምሮ የሚደረጉ ሌሎች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
በታምራት አበራ





All reactions:
27You, Masresha Demissie Eshete, Tsehhay Habte and 24 others