AMN – ሚያዝያ 08/2017
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት “ዘላቂ እና ሕዝብን ማዕከል ያደረገ አረንጓዴ ሽግግር” በሚል ጭብጥ እየተካሄደ ባለው የ2025 ፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ የአየር ንብረት ጥበቃን ለማራመድ አስፈላጊ የሆኑ ሶስት ቁልፍ የተግባር ነጥቦችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ ብለዋል፡፡
አንደኛ የአየር ንብረት ጥበቃ የገንዘብ አቅርቦትን የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት በቂ፣ ተገማች እና ዘላቂ በሆኑ ምንጮች ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ሁለተኛ ዘላቂ ልማትን ለመደገፍ እና የአኅጉሩን ወሳኝ ሥነምኅዳር ጥበቃ ለማድረግ በአለም የኃይል ምንጭ ኢንቬስትመንት ሽፋን ውስጥ የአፍሪካን ድርሻ በአሁኑ ወቅት ካለበት ሁለት ከመቶ በ2030 ወደ ሃያ ከመቶ ማሳደግ ይገባናል።
ሶስተኛ የብዝኀ ሕይወት ጥፋትን እና የምድር መራቆትን በመዋጋት ተፈጥሮን ለመጠበቅ አፋጣኝ ርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ብለዋል፡፡ይኽም እንደ አረንጓዴ አሻራ ያሉ ሕዝባዊ ሥራዎችን በገንዘብ መደገፍን በዚህም ለየአካባቢው ኅብረተሰብ ከአድልዎ የፀዳና ፍትኀዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥን ያካትታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልእክታቸዉ፡፡