የበዓሉ ታዳሚ የውጭ ቱሪስቶች ሌሎች መዳረሻ ስፍራዎችን ይጎበኛሉ- አቶ ስለሺ ግርማ

You are currently viewing የበዓሉ ታዳሚ የውጭ ቱሪስቶች ሌሎች መዳረሻ ስፍራዎችን ይጎበኛሉ- አቶ ስለሺ ግርማ

AMN – ጥር 10/2017 ዓ.ም

የጥምቀት በዓልን ለመታደም ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት የገቡ እንግዶች ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ዕድል መመቻቸቱን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ገለጹ።

አቶ ስለሺ እንደገለጹት መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት አይነተ ብዙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ለምተዋል።

አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ ነባሮችን የማደስ፣ የአስጎብኚ ድርጅቶችን አቅም ማጎልበትና መሰል ተግባራት ተከናውናዋል ብለዋል።

ይህም ለዘርፉ ውጤታማነት እና ለኢትዮጵያ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታ እየፈጠር ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

የቱሪስት መዳረሻዎች የጎብኚዎችን ቆይታ እንዲራዘም እያስቻሉ መሆኑን ገልፀዋል።

ለከተራና ጥምቀት በዓል ወደ ኢትዮጵያ የመጡ በርካታ ጎብኚዎች ከበዓሉ በኋላም ተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ ዕድል መመቻቸቱን ገልጸዋል።

አስጎብኚ ድርጅቶች ከተለያዩ ዓለም ሀገራት የሚመጡ ቱሪስቶችን ተቀብለው ለማስተናገድ በሚሰሩት ስራ ድጋፍ እየተደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review