የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው

AMN – መጋቢት 15/2017 ዓ.ም

በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በተላለፉ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ እና የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዘዳንት አቶ አክሊሉ ታደሰ፣ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ብልጽግና ፓርቲ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች በርካታ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል፤ለዚህም በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም በግብር፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና በሌሎችም መስኮች በርካታ የልማት ውጤቶች መገኘታቸውንም ገልጸዋል።

በቀጣይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት መምከር እና ለገቢራዊነቱም መትጋት ይገባል ብለዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በበኩላቸው፣ እንደ ሀገር ለተገኙ ለውጦች ወጣቶች ትልቅ ሚና ነበራቸው ብለዋል።

በርካታ የፓርቲ እና የመንግስት ስራ ተከናውነዋል፤ ውጤቶችም ተገኝተዋል ያሉት አቶ አለማየሁ

ከወጣቶች ወጪ ጠንካራ ፓርቲ መገንባት አይቻልም፤ ይህንንም መሠረት በማድረግ የወጣቱን ሚና ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።

ወጣቱ አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎችን ገቢራዊ ከማድረግ አኳያ ኃላፊነት እንዳለበት የጠቆሙት ምክትል ኃላፊው እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ለቀጣዩ አቅም ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ መለሰ አባተ መድረኩ የበለጸገች ሀገር ለመፍጠር የተቀመጠውን አቅጣጫ ገቢራዊ ከማድረግ አካያ የወጣቱን ሚና የሚያስቀምጥ ነው ብለዋል።

ይህ መድረግ በመላው ሀገሪቱ የሚካሄድ ሲሆን 5 ሚሊየን ወጣቶች የሚሳተፉበት ነውም ተብሏል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review