የአማራ ክልል መንግሥት ለጎንደር ከተማ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለጎንደር፣ ለባሕር ዳር እና ለደሴ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለእያንዳንዳቸው 100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚሰጥ ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።
በገቢ ማሰባሰብ መርሐ-ግብሩ በርካታ ድርጅቶች እና ግለሰቦችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ 50 ሚሊዮን ብር፣ አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 35 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድረገዋል።
“ኑ ጎንደርን እንሞሽር” የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር እንደቀጠለ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሶማሌ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ሙስጦፋ ሙሐመድ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል እና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።