የአድዋ ድል በህብረት እና በአንድነት ማንኛውንም ተግዳሮት መሻገር እንደሚቻል ማሳያ ነው-የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ

You are currently viewing የአድዋ ድል በህብረት እና በአንድነት ማንኛውንም ተግዳሮት መሻገር እንደሚቻል ማሳያ ነው-የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ

AMN – የካቲት 6/2017 ዓ.ም

የአድዋ ድል በህብረት እና በአንድነት ማንኛውንም ተግዳሮት መሻገር እንደሚቻል ማሳያ ነው ሲሉ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በአድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ መታሰቢያውን ጎብኝተዋል።

በአድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አቀባበል የተደረገላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞተሊ የአድዋን ድል ታሪክ ስጎበኝ የራሴን ሀገር ባርባዶስን ታሪክ ጭምር ነው ያየሁት ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካውያን ብሎም የአለም ጥቁር ህዝቦችን ብቻ ሳይሆን መላው የአለም ጭቁኖች ከጭቆና እንዲወጡ አርዓያ ሆናለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆንም ተጠቃሽ ነች ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቀድሞ ታሪክን በአግባቡ በመሰነድ የማስቀመጡ ተግባር ቀጣይ ትውልድ ከስህተቶች እንዲማር ስኬቶችንም እንዲያስቀጥል የሚያግዝ አርዓያነት ያለው ታሪክ ነውም ብለዋል።

በኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ከተማ ለተደረገላቸው አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።

በሰብስቤ ባዩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review