የአገው ፈረሰኞች በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ አግባብ በድምቀት በመከበር ላይ ነው፡-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

You are currently viewing የአገው ፈረሰኞች በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ አግባብ በድምቀት በመከበር ላይ ነው፡-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአገው ፈረሰኞች በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ አግባብ በድምቀት በመከበር ላይ ነው ፡፡

በመግለጫውም በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ 85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ አግባብ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ብሏል።

የአገው ፈረሰኞች ማህበር ከ62 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን 85ኛው በዓል “አርበኝነታችን ለአሁናዊ ሰላማችን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ እንደሚገኝም ነው ያሳወቀው።

በዓሉን ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዓመታት በተለየ ድምቀት ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ አግባብ፤ በጉጉት የሚጠበቀው የፈረስ ጉግስ፣ ስግሪያ፣ ሽምጥ ግልቢያና በተለያዩ ትርኢቶች እና በሌሎች ዝግጅቶች ከትናንት ጀምሮ እየተከበረ እንደሚገኝም አመልክቷል።

በበዓሉ ሥነ-ሥርዓት ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ አየለ አናውጤ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ አመራር አባላት ተገኝተዋል ብሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review