የኮሪደር ልማት በአማራ ክልል ሰባት ከተሞች በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

You are currently viewing የኮሪደር ልማት በአማራ ክልል ሰባት ከተሞች በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት

AMN – የካቲት 2/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማት በአማራ ክልል ሰባት ከተሞች በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የኮሪደር ልማት በከተሞቹ የራስ ዐቅም፣ ከሕዝብ ተሳትፎ፣ ከፌደራልና ከልዩ ልዩ ድጋፎች በሚገኝ ዐቅም እየተተገበረ እንደሚገኝም አመልክቷል

በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ እና ወልድያ ከተሞች ተጀምሮ 32.23 ኪ.ሜ መንገድ 27.04 ሄር አረንጓዴና ፓርክ ልማት፣ 3.7 ሄ/ር የሕዝብ አደባባይ፣ 25 ኪ.ሜ የመንገድ ዳር መብራትና ሕንፃ የማስዋብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉም ብሏል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከተለመደዉ የፕሮጀክት አፈጻጸም በተለየ ሁኔታ በተለያዩ ምእራፎች ተከፋፍሎ በአጭር ጊዜ ጥራቱን ጠብቆ እየተተገበረ መሆኑንም ጠቁሟል።

ጎንደር፣ ኮምቦልቻና ባሕርዳር ከተሞች የመጀመሪያ ምእራፍ በማገባደድ ወደ ሁለተኛ ምእራፍ ሥራዎች በመሸጋገር ላይ ናቸዉም ብሏል፡፡

በዚህ የኮሪደር ልማት እንደ ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሉ ከተሞች ግራ እና ቀኝ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መንገድ፣ ፐብሊክ-ፕላዛ (ማረፊያና መዝናኛ)፣ የመጸዳጃ ቤቶችና ዘመናዊ ካፍቴሪያዎች እየተገነቡ መሆኑንም አመልክቷል።

በግራ እና ቀኝ ከ5 ሜትር በላይ ስፋት ያለዉ አረንጓዴ ልማት መከናወኑንና የሐይቅ ዳርቻውን ለሕዝብ የመክፈት ሥራ መሰራቱንም ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በመልእክቱ አስታውቋል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review