የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ

You are currently viewing የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ ምዝገባ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በወቅታዊ እና በሐጅ ምዝገባ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሃጅ ኢብራሂም ቱፋ በሰጡት መግለጫ፣ የዘንድሮው የሐጅ ምዝገባ እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ሐጅ ምዝገባ በሳውዲ ሐጅ ሚኒስቴር መመሪያና ፍቃድ መሠረት የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰው፣ ምዝገባው እስከ መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ተናግረዋል።

የሀጅ ምዝገባ በመላ ሀገሪቱ በ30 የምዝገባ ጣቢያዎች በቴክኖሎጂ ታይግዞ እየተከናወነ ይገኛል።

በዘንድሮው የሐጅ ጉዞ 10 ሺህ ሁጃጆችን ለመውሰድ መታቀዱም ተገልጿል።

እስካሁን ያልተመዘገቡ የሐጅ ተጓዦች በቀሪው ጊዜ ሳይዘናጉ እንዲመዘገቡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ በኩል የተወሰኑ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያው የህዝቡን አብሮነት፣ አንድነት እና ፍቅርን ለመሸርሸር እየሰሩ ቢሆንም ሙስሊሙና ክርስቲያኑ ችግር ፈጣሪ አካላትን ለህግ በመተው አብሮነታቸው እና አንድነታቸውን ሊያጠናክሩ እንደሚገባ መልዕከት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ የበርካታ የጋራ እሴቶች ባለቤት መሆኗን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ ይህንን ለመሸርሸር የሚንቀሳቀሱ አካላትን ሁሉም ሊያወግዝ ይገባል ብለዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review