AMN- ጥር 22/2017 ዓ.ም
የዚምባቡዌው ዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ የብሔራዊ ውጭ ግንኙነት ዋና ጸሃፊ ሲምበርሼ ሙቤንጌግዊ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ዋና ጸሀፊው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደረሱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ከነገ ጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡