የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

You are currently viewing የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ

AMN- ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አደረገ።

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደገለጹት በዘንድሮ አመት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚቀላቀሉ ተማሪዎች በደረጃ አንድና ሁለት የሚመዘገቡ ሲሆን በአስራ ሁለተኛ ብሄራዊ ፈተና ወንዶች 141 እና ከዚያ በታች፣ ሴቶች 138ና ከዚያ በታች ያመጡ ናቸው።

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 137ና ከዚያ በታች፣ ለሴቶች 134ና ከዚያ በታች፣ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 124ና ከዚያ በታች መሆኑንም ገልጸዋል።

በደረጃ ሶስትና አራት የሚመዘገቡ በ12ኛ መልቀቂያ ፈተና ወንዶች 142ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 139ና ከዚያ በላይ ያመጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ለታዳጊ ክልሎችና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንዶች 138 እናና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች 135ና ከዚያ በላይ፣ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 125ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ናቸዉም ብለዋል።

በደረጃ አምስት የሚሰለጥኑ ወንዶች 179ና ከዚያ በላይ፣ሴቶች 170ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ይሠለጥናሉ ተብሏል።

ከታዳጊ ክልሎችና ከአርብቶ አደር አካባቢዎች ወንዶች 167ና ከዚያ በላይ፣ ሴቶች 162ና ከዚያ በላይ እንዲሁም ከሁሉም ከልል አካል ጉዳተኞች 154ና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት በደረጃ አምስት ገበተው መሠልጠን እንደሚችሉ ሚኒስትር ዴኤታዉ አብራርተዋል።

በአጠቃላይም በዘንድሮዉ አመት ከ526 ሺ 683 ተማሪዎች የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆችን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሚንስቴሩ ስልጠናን ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራን እንዳጠናቀቀም አስታዉቋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review