110 የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ

You are currently viewing 110 የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች የመኖሪያ ቤት እጣ አወጡ

AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም

110 የካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች በዛሬው እለት የመኖሪያ ቤት እጣ አውጥተዋል፡፡

ለካዛንቺስ የልማት ተነሺዎች ዘመናዊነቱን የሚመጥን ምትክ ቤት የመስጠት ሂደቱ እንደቀጠለ ነው።

ይህ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አዲሱ ሻንቆ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ተጠቃሚ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ካዛንቺስ መሆኑንም አመላክተዋል።

ካዛንቺስን መልሶ በማልማት ስሟን የሚመጥን ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እና የክፍለ ከተማው ከፍተኛ አመራሮች ሌት ተቀን መትጋት ከጀመሩ ወራትን እንዳስቆጠሩም አንስተዋል።

የኮሪደር ልማቱ ዋና ዓላማ ከተማን ከመቀየር ጎን ለጎን የነዋሪውንም አኗኗር ማዘመንን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ፣ የካዛንቺስ ነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየር ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ከማቅረብ ጀምሮ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ የማሟላት ስራ በፍትሃዊነት እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

ይህ መልካም ተግባር በከፍተኛ አመራሩ መልካም ፍቃድና ውሳኔ ብቻ ሳይሆን በህዝቡ ተሳትፎም ጭምር የሚከናወን መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

ለአብነትም ከነዋሪው ጋር የሚደረገው ምክክር፣ የቤት እጣ አወጣጥ ፍትሃዊነት እና የቅሬታ አቀራረብ ሂደት፣ የከፍተኛ አመራሩ የየእለት ክትትል እና ድጋፍ፣ እንዲሁም ሌሎች በጎ ተግባራት ምስክር እንደሆኑ መግለፃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review