ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በገላን ጉራ ላደረጉት ጉብኝት ምስጋና አቀረቡ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በገላን ጉራ ላደረጉት ጉብኝት ምስጋና አቀረቡ

AMN – ሚያዝያ 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከዚህ በፊት ካዛንችስ ይኖሩ የነበሩ ጎረቤቶቻቸውን በገላን ጉራ በመገኘት ጎብኝተው እንኳን ለትንሳኤ በአል አደረሳችሁ ብለዉ ማእድ አጋርተዋል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ላደረጉት ጉብኝት እና ማእድ በማጋራታ ለነዋሪዎች ላስተላለፉት የበዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review