ፓሪሰን ዠርማ ከ ኢንተር ሚላን ያደረጉት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ብዙዎች ባለገመቱት መንገድ ተጠናቋል።
በወጣቶች የተገነባው ፓሪሰን ዠርማ ልምድ ያካበቱትን ኢንተርሚላኖችን 5ለ0 አሸንፈዋል።
የፓሪሱ ክለብ አብዝቶ የተመኘውን ዋንጫ በምርጥ ብቃቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳክቷል።
ፓሪሰን ዠርማን አችራፍ ሃኪሚ ፣ ዴዝሪ ዱኤ ሁለት ፣ ኽቪቻ ክቫራስሄሊያ እንዲሁም ሴኒ ማዩሉ ያስቆጠሯቸው ግቦች ባለድል አድርገውታል።
የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በማንሳትም ከማርሴይ ቀጥለው ሁለተኛ የፈረንሳይ ክለብ ሆኗል። የክለቡ ኳታራዊያን ባለቤቶችም ምኞታቸው እውን ሆኖላቸዋል።
ስፔናዊ አሰልጣኝ ሊውስ ኤነሪኬ ከ10 ዓመት በፊት ከባርሰሎና ጋር ያሳካውን የቻምፒየንስ ሊግ ድል ከፒ ኤስ ጂ ጋር ደግሞታል።
ኤነሪኬ ልክ በባርሰሎና እንዳደረገው የሶስትዮሽ ድልም ጭምር አሳክቷል።
በሲሞኒ ኢንዛጊ እየተመሩ ጥሩ ጉዞ ያደረጉት ኢንተር ሚላኖች የውድድር ዓመቱን ያለምንም ዋንጫ አጠናቀዋል።
በሸዋንግዛው ግርማ