በተለምዶ የሿሿወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing በተለምዶ የሿሿወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

AMN ሰኔ 10/2017

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ የሿሿወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ በቂርቆስ፣ በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ፣በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በልዩ ልዩ ስፍራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ አስራ አንድ አባላት ያሉት ሁለት ቡድኖችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኤኤምኤን ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀል ለመስራት ይገለገሉባቸው የነበሩ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 53234፣ ኮድ 3 ኦ/ሮ 50777 እና ኮድ 2 አ/አ B 50438 ተሽከርካሪዎችን መያዙንና ከዚህ ቀደም በፈፀሙት የሿሿ ወንጀል አስፈላጊው ማስረጃ ተሰብስቦ አራት የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review