እስራኤል በተኩስ አቁሙ መስማማቷን አስታወቀች

You are currently viewing እስራኤል በተኩስ አቁሙ መስማማቷን አስታወቀች

AMN – ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ ዙሪያ እስራኤል መስምማቷን የተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

እስራኤል ስኬታማ በነበረው በአንበሳው መነሳት ዘመቻዬ የኢራንን የኑውክሌር ጦር መሳሪያ እና ባለስቲክ ሚሳኤል ስጋት ያስወገድኩ በመሆኑ በቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብ ላይ ተስማምቻለሁ ማለቷን ቢቢሲ እና ኤቢሲ ኒውስ ዘግበዋል።

የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመላክተው መግለጫው አሜሪካ የኢራንን የሊውክሌር ስጋት ለመቀነስ ላደረገችው ድጋፍ እስራኤል ዶናልድ ትራምፕን ማመስገኗን አካቷል።

የኢራን ቀጣይ እርምጃ ምን ይሆናል የሚለው እየተጠበቀ የሚገኝ ሲሆን፤ በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የሰነዘርኩትን ስኬታማ ጥቃት ተከትሎ የተኩስ አቁም ስምምነቱ በአስገዳጅነት በእስራኤል ላይ ተጥሏል ብላ ነበር።

በተጨማሪም ኢራን እስካሁን ከእስራኤል ጋር የተደረገ ምንም አይነት የተኩስ አቁም ስምምነት የለም በማለት ማስተባበሏን እና እስራኤል ጥቃቷን ካቆመች እኔም የጥቃቴን ፍፃሜ አደርጋለሁ ማለቷን አልጀዚራ ዘግቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review