መንግስት ከተሞችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት እንዳስደመማቸው የሚዲያ ባለሞያዎች እና ማህበራዊ አንቂዎች ተናገሩ

You are currently viewing መንግስት ከተሞችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያከናወናቸው ተግባራት እንዳስደመማቸው የሚዲያ ባለሞያዎች እና ማህበራዊ አንቂዎች ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN – ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

በተረሱ ቀደምትና ጥንታዊ ከተሞች እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አድናቆትን እንደፈጠሩባቸው በጉብኝቱ የተሳተፉ ባለሙያዎች ተናረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር ) ከመላው ኢትዮጵያ ከተዉጣጡ የህዝብ እና የግል ሚዲያ ባለሞያዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት የተሳተፉ ባለሞያዎች ከውይይቱ በመቀጠል በሀገሪቱ በተለያዩ ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማቶች፤ የተገነቡና በግንባታ ላይ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችንና ታሪካዊ ስፍራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጅማ ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ጅማ ከተማን በስራ አጋጣሚ እንደሚያውቋት ገልፀው አሁን ላይ የተሰራው የኮሪደር ልማት ግን ከተማዋን ለቱሪስት ምቹ እንድትሆን ማድረጉን እና በተሰሩት ስራዎችም መደመማቸዉን ተናግረዋል፡፡

የልማት ስራዎቹ በከተማና በገጠር የሚኖሩ ዜጎችን ህይወት ያስተሳሰሩና የቀየሩ መሆናቸዉንም ገልጸዋል፡፡

መንግስት የቱሪዝምን ዘርፉን ለማዘመንና ለማስፋት እየሰራቸው ያሉ ስራዎች በተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸዉን በጅማ ከተማ የተሰሩ ስራዎች ማሳያ ነው ያሉት ባለሞያዎቹ ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የልማት ስራዎቹ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን ከማድረግ ባለፈ በስራ ዕድል ፈጠራና የጎብኝዎችን ቆይታ ከማራዘም አንጻርም ከፍተኛ ሚና እንዳላቸዉ ባለሞያዎቹ አብራርተዋል፡፡

በጅማ ፤ በጎንደር ፤ በወንጪ እና በሃላላ ኬላ ለቀጣዩ ትዉልድ ተስፋ የሚሆኑ በርካታ የልማት ስራዎች መሰራታቸዉን መመልከታቸዉን ነዉ ባለሙያዎቹ የገለጹት፡፡

መንግስት የከተሞችን ገፅታ በመቀየር ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግና የቱሪዝሙን ዘርፍ ለማሳደግ ከሚያከናውናቸው ስራዎች በተጨማሪ ሌሎች የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ሃገርን የሚያሻግሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከተጣለባቸዉ ሙያዊ ሃላፊነት አንጻር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ፤ የኔነት ስሜት እንዲፈጠር ለማድረግ እና በሞያቸው ሃገራቸውን ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩም የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎቹ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

AMN

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review