ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ነገ በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ነገ በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ይሰጣሉ

AMN- ሰኔ 25/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ነገ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ የሚገኙት የመንግሥታቸውን የ2017 የዕቅድ አፈፃፃም አስመልክቶ የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚያነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ያዕቆብ ወልደ ሰማያት ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት በጉባኤው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች፤ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ይገኛሉ፡፡

ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ነገ ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከ2፡30 ሰዓት ጀምሮ ይካሔዳል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

a

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review